Alemnew mekonnen biography of barack
Alemnew mekonnen biography of barack gas...
Alemnew mekonnen biography of barack
የመማር ተስፋን ያጨለመው ትውልድ ተሻጋሪ ቀውስ፤ እንዴት ይታከም?
ተማሪ ምስጋናው ስንታየው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ጎጃም ዞን ይልማና ዴንሳ ወረዳ መሰቦ ቀበሌ ነዋሪ ነው። በአዴት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ 9ኛ ክፍል ትህምህርቱን መከታተል የቻለ የ18 ዓመት ታዳጊ ወጣት ነው። ይሁንና በአሁኑ ወቅት በክልሉ በመንግስት የጸጥታ ኃይልና በፋኖ ታጣቂ መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት አዘል ግጭት ሳቢያ ትምህርቱን መቀጠል ባለመቻሉ ቤተሰቡን በስራ እያገዘ ይገኛል።
ከብት ከሚያግድበት ቀዬ በአባቱ አርሶ አደር ስንታየሁ ሁነኛው ጥሪ ዶይቼ ቬለ ለቃለ-መጠይቅ ያገኘው ተማሪ ምስጋናው፤ ትምህርቱን ከ9ኛ ወደ 10ኛ ክፍል በ ዓ.ም.
ያለፈ ቢሆንም ዓ.ም. ላይ «አገር ሰላም ባለመሆኑ» የ10ኛ ክፍል ትምህርቴን መቀጠል አልቻልኩም ሲል ነግሮናል።
ተማሪው ተምሮ ዶክተር የመሆን ትህልም ሰንቋል። ዶክተር መሆን የምፈልገው «ህዝብ ለማከም ነው» የሚለው ተማሪ ምስጋናው «ከትምህርት ሰላም ይቀድማል፤ ሰላም ከሌለ ትምህርት መቀጠል አይቻልም።» በሚል ሰላም በአካባቢው ባለመኖሩ የመማር ህልሙን እንዳጨለመበት ይናገራል።
ተማሪ ስንታየውን ጨምሮ 5 ልጆች ያላቸው አርሶ አደር ስንታየው ልጃቸው ወደ 5 ኪሎ ሜትር ተጉዞ አዴት እየተማረ እንደነበር በማስታወስ በጦርነቱ ምክኒያት ትምህርት እንደተቋረጠ ይናገራሉ። «እያለፈ ያለው የንፁሐን ሕይወት ነው፤ ይህም የተማሪ ልጆቻችንን ስነ-ልቦና እንዲሟሽሽ አድርጓል» ሲሉ የቀጠሉት አርሶ አደሩ ሌሎች ሶስት ልጆቻቸውም ትምህርት ጨርሰው ስራ አጥተው እቤት መቀመጣቸውን ይናገራሉ።
አቶ በላይ (ስማቸው የተቀየረ) በክልሉ ምህራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ ባለትዳርና የ4 ልጆች አባት ናቸ